LNB ምንድን ነው?

 LNB ምንድን ነው?


▬▬▬▬▬▬▬▬
 . LNB ምንድን ነው?
LNB የእንግሊዝኛ አህፅሮተ ቃል ሲሆን ሲተነተን (Low Noise Block )የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ይይዛል።
LNB የራዲዮ ሞገድን ከዲሽ ላይ በመቀበል ወደ ሲግናል ከቀየረ በኋላ በኬብል አማካኝነት ወደ ሪሲቨሮች የሚልክ ዲሽ አናት ላይ የሚገጠም መሳሪያ ነው ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➋. የLNB አይነቶች ስንት ናቸው?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በመሠረታዊነት አገራችን ውስጥ የሚስተዋሉት የLNB አይነቶች ሁለት ቢሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች ግን በዓለም ላይ 4 እና ከዚያ በላይ እንደሆኑ ያስረዳሉ።
ለመሆኑ አገራችን ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉት የLNB ዓይነቶች እነማን ናቸው እስኪ እንመልከታቸው። ብዙ ሰዎችም በእነዚህ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ሲያወዛግባቸው እንመለከታለን።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሀ. KU Band LNB
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በተለምዶ Ku band የሆኑ ፍሪኩየንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነው።
12522
ባህሪያቸው
▬▬▬▬
ባለ 5 ዲጅት ፍሪኩየንሲን ይቀበላል።
የፍሪኩየንሲ ወሰኑ ከ11700-12220 GHzነው።
ትልቅ የፍሪኩየንሲ መጠን መያዛቸው አጭር የሞገድ ርዝመት አንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
በአጭር ሞገድ ርዝመት መስራታቸው በትንንሽ ዲሾች (offset dishes) እንዲሰሩ አስችሏቸዋል።
ለምሳሌ፦(ዲያሜትራቸው ከ30-65ሳ.ሜ የሆኑ ዲሾች ላይ እንዲሰሩ አስችሏቸዋል።)
በዚህም የተነሳ ብዙ አገራትን የማይሸኑ ከመሆናቸውም በላይ ለተለዋዋጭ የአየር ጸባይ ተጋላጭ ናቸው።
(ለምሳሌ:- እንደ ዝናብ እርጥበት አዘል አየር....ወዘተ)
በLNBው ውስጥ የሚኖረው የርግብግቦሽ (oscillation) መጠን ከፍ ሲል 10600 እንዲሁም ዝቅ ሲል 9750 ነው:: አለማቀፋዊ የሆኑ KU Band LNBዎች የLNB freq 9750/10600 ነው።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ለ. C Band LNB
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በተለምዶ C band የሆኑ ፍሪኩየንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነው።
4103
ባህሪያቸው
▬▬▬▬
ባለ 4 ዲጅት ፍሪኩየንሲን ይቀበላል።
የፍሪኩየንሲ ወሰኑ ከ3700-4200 GHzነው።
ትንሽ የፍሪኩየንሲ መጠን መያዛቸው ረጅም የሞገድ ርዝመት አንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
በረጅም ሞገድ ርዝመት መስራታቸው የግዴታ ትልልቅ መጠን ላቸው ዲሾችን (prime focus dishes) እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል።
ለምሳሌ ፦(ዲያሜትራቸው ከ180-240ሳ.ሜ የሆኑ ዲሾች ላይ እንዲሰሩ አድርጓቸዋል።)
ይህም የሳተላይት ሽፋኑ ብዙ አገራትን እንዲያካልል ከማገልገሉም በላይ ለተለዋዋጭ የአየር ፀባይ እንዳይጋለጡ አግዟቸዋል ።
ብዙ አገራትን እንደማካለላቸው መጠን አብዛኛዎቹ ቻናሎች አለማቀፋዊ ቋንቋን ይጠቀማሉ ይዘታቸውም በዚያው ልክ መልካም የሚባል ነው።
በLNBው ውስጥ የሚኖረው የርግብግቦሽ (oscillation) መጠን አንድ ጫፍ ሲሆን 5150 ነው::
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍

Post a Comment

0 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.