🛑NanoTechnology🛑ምንድነው?

🛑NanoTechnology🛑

NanoTechnology ምንድነው?
Nano Technology ሌላ ተአምር ሳይሆንv እየተጠቀምን የምንገኛቸውን ቴክኖሎጂዎች አሁን ካሉበት size እንዲያንሱ ለማድረግ መሞከር ነው።

ለምሳሌ ያክል የመጀመርያው ENIAC ኮምፒውተር አንድ ክፍል ይሞላ እንደነበር ሲነገር እንሰማለን! Transistors እና Integrated Circuit( IC ) ከተፈጠረ በኋላ ግን አሁን ያለውን መጠን ሊይዝ ችሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲ ደሞ በ Nano Technology ከዚህ በጣም በብዙ እጥፍ አሳንሶ ለመስራት እየተቻለ ነው።
Nano ማለት የ ግሪክ ቃል ሲሆን "Dwarf" ወይም ድንክ ማለት ሲሆን በ ማትስ ቀመር ደሞ ከ Micro ቀጥሎ የሚገኝ የ አንድ አንድ Billion (10^-9) ነው።

በየትኛው ዘርፍ ላይ ይገኛል?

ይሄ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ትልቅ ዕምርታ እያሳየ ሲሆን እንዲሁም በ መኪና እና በ አውሮፕላን ኢንደስትሪ ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።

📲 ከሞባይል ጋር ምን አያያዘው?

አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው ይሄ ቴክኖሎጂ ለስልኮችም ገጸ በረከት ይዞ እየመጣ ነው። ለስልክ ስክሪኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።

✍️ እንዴት ስልክ ላይ ይሰራል❓

✍️🤭እንኳን ወደ silicon dioxide Sio2 አለም በሰላም መጣቹ።
እንዴት መሰላቹ መስታወት የሚሰራው ከ Sio2 ነው። በፈሳሽ መልክ የሚመጣው ይሄ element በስልኮቻችን ላይ ይቀቡና እንዲደርቁ ይደረጋል። ✍️🖥ከደረቀ በኻላ ያለው ቅጥነት 100nm እንደሆነ ይነገራል ይሄም በአይናችን ለማየት አዳጋች ነው። እንግዲህ ይሄን ነው በየመንገዱ እና በየሱቁ እየለጠፉ ያሉት!

         🔧 ያለው ጠቀሜታ 🔧
🔅እንደ ግላስ መለጠፉ በአይን ስለማይታይ የስልካችንን ውበት አይቀንሰውም።
🔅Scratchን እጅግ በጣም መቋቋም ይችላል። ይሄንንም መሞከር ይቻላል።
🔅WaterProof በመሆኑ ውሃ አያስገባም። 🔅እንዲውም ቆሻሻ አይይዝም።
🔅Uv Light መቋቋም ይችላል
🔅በጣም ለስላሳ በመሆኑ ተች ለማድረግ እንደ ግላስ አያስቸግርም!

       ❌❌ ችግሮቹ❗️❌❌

✍️ እዚጋ ማየት ያለብን አንዳንድ ፔጆች Fake ነው የሚል ነገር ሲይፉ አያለው ምክንያት ሲጠየቁ የተሰበረባቸው ሰዎች አሉ የሚል ነው። ይሄ ቴክኖሎጂ የሚሰራው ለስልካችን Digitizer ወይም Touch ነው እንጂ ውስጥ ያለውን screen አያጠነክረውም። ስክሪን በባህሪው ፈሳሽ በመሆኑ ከከፍታ ቦታ ሲወድቅ የመፍሰስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ሌላኛው ደሞ ምናልባት አጭበርባሪዎች ተመሳሳይ fake ኬሚካል እየተጠቀሙ ሊሆን ይችላል። እኔ ለምሳሌ ተጠቃሚ ነኝ ስልኬን በተለያየ ነገር ተቹን በመምታት ቼክ አርጌዋለው ምንም ነገር ገደብ ስላለው ከዛ ፎርስ በላይ ስንጠቀም ብረትም እንደሚጣመመው ይሄም ሊሰበር ይችላል።

✍️ ሌላ ችግር ሰሞኑን በየሚዲያው እየሰማን ያለነው ካንሰር ያመጣል የሚለው ነው። ይሄ በጥናት ያልተረጋገጠ እና የጨረራ መስሪያ ቤት ጥናት አላደረኩም ያለ ሲሆን ምናልባት ጥናት አድርጎ ይፋ ቢያደርገው ካሉባልታ ወሬ ይታደገናል። የጨረራ መስሪያ ቤት " በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታውቋል!

ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ መፈተሽ እንዳለበት የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሺፈራው ገልፀው በፍተሻውም ወቅት በስልክ ገጽ ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ጨረራ አለው ወይስ የለውም፤ የጨረራ ይዘቱ ምን ያህል ነው የሚለው ፍተሻ እንደሚደረግበት ለEBC ገልጸዋል ።" ይሄን ነው እንግዲህ የገለጸው በሌላ በኩል ደሞ የ AP ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ሰማውት ባለው ይሄን ጽሁፍ አስፍሯል

" እኔ ደግሞ በደረሰኝ መረጃ ፈሳሹ "ስልክ እንዳይሰበር ያደርጋል" ተብሎ የሚተዋወቀው ውሸት እንደሆነ ከአንድ የፈሳሹ አስመጪ ጭምር ተነግሮኛል።
በነገራችን ላይ ይህ መሳርያ እና ፈሳሽ እስከ 12,000 ብር ይሸጣል፣ ፈሳሹን ስልክ ላይ ለማስቀባት ደግሞ እስከ 250 ብር ይጠየቃል።"

🚫🚫NB፦ ይሄን ፕሮግራም ለመስራት ሳስብ ብዙ ድረገጾች ላይ የተለቀቁ ጽሁፎችን ለማንበብ ሞክሬያለው እንዲሁም ስልካቸውን ያሰሩ ሰዎችን ለመጠየቅ ሞክርያለው ይሄ ነው የሚባል ትልቅ ችግር አላነበብኩም አልሰማውም። ምናልባት ከኔ የተሻለ መረጃ ያለው ካለ ችግሮችን በማስረጃ አስደግፎ ሊነግረን ይችላል።

Post a Comment

0 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.