የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ከሆኑ ማወቅ ያለቦት ወሳኝ ነገሮች!!

እርስዎ የበይነመረብ ፣የድረ-ገጽ አልያም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ከሆኑ ማወቅ ያለቦት ወሳኝ ነገሮች!!


     ❍✰✰✰✰✰◉⚇◉✰✰✰✰✰❍
🌟እርስዎ በማያውቁበት ሁኔታ
የቴክኖሎጂ ተቋማቱ በስልክዎ አማካኝነት የት እንዳሉ የመለየት፣የሚላላኩትን መልእክቶች ስካን አድርጎ ማስቀረት እና የእርስዎን መረጃ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ መሰጠቱን ያውቃሉ?
✔ቢቢሲ በጉዳዩ ባደረገው ጥናት መሰረትም እነዚህ ተግባራትም በግላዊነት ፖሊሲዎቻቸው ላይ አብዛኛዎቹ የሰፈሩ ሲሆን የተጠቀሙበት ቋንቋዎች ለመረዳት አብዛኛዎቹ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ሚያስፈልጋቸው አይነት ናቸው ብሏል፡፡
👉የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እኛ ባልተረዳንበት ሁኔታ ከሚተገብሯቸው ነገሮች መካከልም የሚከተሉት ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡
▣ያሉበት መዳረሻ በክትትል ውስጥ መሆኑ ፡-አብዛኛዎቹ መተግበሪያዎች (apps) እርስዎን ያሉበትን ስፍራ በስልክዎ ላይ በተጫነው የጂፒኤስ (GPS) አማካኝነት ማወቅ የሚችሉበትን
ፍቃድ የሚጠይቁ ቢሆንም ተጠቃሚዎች ባይፈቅዱ እንኳ መረጃዎችን ይሰበስባሉ፡፡ በምሳሌነት ከሁለት ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክ ከአቅጣጫ ጋር ግንኙነት ያለቸውን
መረጃዎች በስልክዎ ጂፒኤስ አማካኝነት ይሰበስባል፡፡ ቲዊተርም ያሉበትን አካባቢ መረጃ ይጠይቃል፡፡
◉የቴክኖሎጂው ኩባንያዎች የእርስዎን መረጃ ለተባባሪ ኩባንያዎች አሳልፈው ይሰጣሉ፡-እርስዎ የአጠቃቀም ደንብ እና መመሪያዎችን በሚስማሙበት ወቅት እርስዎ በወቅቱ መረጃውን ለጠየቀዎ እና ለሞሉለት መተግበሪያ ብቻ አለመሆኑ እና ሌሎች አካላትም የሚካፈሉት መሆኑ
◉በሶስተኛ ወገን የአጠቃቀም መመሪያ መገዛት፡-የቴክኖሎጂ ተቋማትን የአጠቃቀም መመሪያ ማንበብ እና መተግበር በቂ አለመሆኑን እና የሌሎችንም ከእርስዎ መረጃ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኩባንያዎች አጠቃቀም መመሪያ ማየት ግድ ነው፡፡
✔👉ለምሳሌ አማዞን የእርስዎን የግል መረጃ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ እንደሚሰጥ በአጠቃቀም መመሪያው ላይ አስፍሯል፡፡
◉ቲንደር(Tinder) የተባለው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ ከስምዎ፣ከእድሜ እና መዳረሻ በተጨማሪ የተጠቃሚዎችን የእንቅስቃሴ መጠን እና መዛነፍ ሁሉ የመረምራል፡፡
◉እርስዎ የሰረዙትን የፍለጋ ዝርዝር አለመወገዱ፡ ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ እርስዎ ከዚህ ቀደም የተጠቀሙት የፍለጋ ታሪኮችን በሲርዙም በአጠቃቀም መመሪያው ላይ ባስቀመጠው መሰረት እርስዎ የሰረዙት የፍለጋ ዝርዝር ለ6 ወራት ተቋሙ ያስቀምጣቸዋል፡፡
◉የሚጠቀሙበትን የስልክዎን መተግበሪያ እንኳ ቢያጠፉ እንቅስቃሴዎ ክትትል ውስጥ መሆኑ፡ ፌስቡክን የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች እርስዎ የፌስቡክ አባል ሆነው ባይመዘገቡ እንዲሁም የፌስቡክ አካውንት ባይኖሮት እንኳ እንቅስቃሴዎን ይቆጣጠራል፡፡
▣ሊንክድኢን( LinkedIn) የተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ደግሞ የተጠቃሚዎቹን የግል የመልእክት ልውውጦች ስካን አድርጎ ይይዛል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያዉም በአጠቃቀም መመሪያዎቹ ላይ የሚላላኩትን መልእክቶች በአውቶማቲክ ስካነር አማካኝነት ስካን እንደሚያደርግ አሳውቋል፡፡ ቲዊተር ደግሞ በመልእክቶቹ መሃል የመግባት፣የማከማቸት እና ፐሮሰስ ያደርጋል
▣አንዳንድ መተግበሪያዎች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠቃሚዎች በወላጆቻቸው ታዳጊዎቹ የሚጠቀሙዋቸውን ነገሮች ክትትል እንዲያደርጉ ይጠቃሉ።
◉በእንግሊዝ ያሉ ተጠቃሚዎች በአሜሪካ የተከለከሉ ምርቶችን ለማንኛውም አላማ እንዳይጠቀሙ የሚያገድ አንቀጽ አይፎን ለእንግሊዝ ደንበኞቹም እንዲያሰፈር አድርጋለች፡፡
Share and Like Comments
                       ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

ዌብሳይታችን 👉www.tesfatchnical.blogspot.com
ቴሌግራማችን 👉 http://t.me/Tesfatechnical Blog/
ፌስቡክ ፔጃችን 👉 http://facebook.com/tesfatechnical
                    ══════❁✿❁ ══════
➹share

Post a Comment

0 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.