በፍፁም ዳውንሎድ መደረግ የሌለባቸው አፕሊኬሽኖች ልጠቁማችሁ!!

 

source image-clipground.com

መቼስ በዚህ ወቅት ጫኑኝ የማይል የስልክ መተግበሪያ የለም። ዓለም ራሷ የስልክ መተግበሪያዎች ውስጥ ተከናንባ እየገባች ይመስላል።

የደም ግፊት መጠንን ከሚለኩት ጀምሮ ቋንቋ መማሪያዎች፣ ቀን መቁጠሪያዎች፣ ቁርስ ምሳ ማዘዣዎች፣ ታክሲ መጥሪያዎች፣ ባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀሻዎች፤ ብቻ የሌለ ዓይነት የስልክ መተግበሪያ የለም።

ፈተናው ሐሰተኛውን ከእውነተኛው መለየት ነው። በዚህ በኩል እኛ እንርዳዎት! የሚከተሉት ሦስት የስልክ መተግበሪያዎችን ጫኑ ማለት መከራን ስልክዎ ላይ ጫኑ እንደማለት ነው።

ስልክዎን ለጤና መቃወስ የሚያጋልጡ ሐሰተኛ መተግበሪያዎች (Apps) የሚከተሉት ናቸው።

1.የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ

የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ!

የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን “የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም” ይላል።

ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ። 

የስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን “ናይት ሞድ” ወይም “ባትሪ ቆጥብ” የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት።

ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው።

2.ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች

ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። “ክሊን ማስትር” የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው።

ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው “ክሊን ማስተር” የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል።

ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል።

Post a Comment

1 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.