በሞባይል ስልክዎ በሚላክልዎ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መረጃ ከስልክዎ መመዝበር እንደሚቻል ያዉቃሉ?

በሞባይል ስልክዎ በሚላክልዎ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መረጃ ከስልክዎ መመዝበር እንደሚቻል ያዉቃሉ?


♨️በሞባይልስልኮቻችንወይም በተለያዩ ኤሌክትሮኒክ መገልገያዎቻችን ላይ በኤስ ኤም ኤስ # SMS መልዕክት አማካኝነት የሚፈጸሙ የመረጃ ጥቃትን ለመከላከል፤

♨️ ከማናውቀው ሰው መልዕክቶች ከሊንኮች ጋር በሚላኩልን ጊዜ በፍጥነት ከመክፈት መቆጠብ፡፡ በተለይ የተላከው የሊንክ አድራሻ ትክክለኛነት ማረጋገጥ መቻል አለበት፤ ለምሳሌ ዶሜን ኔም(domainname)፣ሆስትናአጠቃላይ ዩ አር ኤል(URL)ደህንነቱንማዎቅ ያስፈልጋል፤

♨️ ለማንኛውም ዓይነት ግላዊ የፋይናንስ መረጃዎቻችንን ለሚጠይቁን መልዕክቶች ምላሽ ከመስጠት መቆጠብ ያስፈልጋል፤

♨️ ስለምንሰራቸው የቢዝነስ እሴቶቻችን እንዲሁም አብረውን በሽርክናና በተለያዩ ዘዴዎች ስለምናከናውናቸው መረጃዎች ለሚጠይቁ አጭር የጽሁፍ አጭር የፅሁፍ መልዕክቶች ከመመለሳችን በፊት ወደ አጋሮቻችንን በመደወል ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ያሥፈልጋል፤

♨️ የሚላኩልን መልዕክቶች ከማናውቃቸው ቁጥሮች ከመሆናቸውም በተጨማሪ አስቸኳይ የሆነ ምላሽን የሚጠይቁን ከሆኑ መመለስ የለብንም፤

♨️ ከማናውቃቸው የኤስ ኤም ኤስ ቁጥሮች በብዛት መልዕክቶች የሚላኩልን ከሆነ የቁጥሮቹን ህጋዊነት ወደ ቴሌ በመደውል ማረጋገጥና ካልፈለግናቸው እንዲቋረጡ ማድረግ ያስፈልጋል፤

♨️ እንኳን ደስ ያላህ/ያለሽ፤ አሸናፊ ሆነሃል/ሆነሻል በማለት ወደ ማናውቀው ስልክ እንድንደውል ከሚሞክሩ አጭበባሪዎች ራሳችንን መከላከል ያስፈልጋል፤

♨️ የሚላኩልን መልዕክቶች የተላኩበትን ጊዜ መቼና ስንት ሰዓት የሚሉትን ጉዳዮች በመመልከት የተላከው መልዕክት ባልተለመደ ሰዓት ከሆነ ከመመለስ መቆጠብ ያስፈልጋል፤

♨️ በኤስ ኤም ኤስ የባንክ አካውንታችንን በተመለከተ ለምንጠየቀው ማንኛውም መረጃ መልስ ከመስጠታችን በፊት በባንክ አካውንታችን ላይ ለተጠቃሚዎቹ የተቀመጡትን ህግና ስርዓቶች መመልከትና ማስታዎስ ያስፈልጋል፡፡
ይህን በማድረግዎ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ ይችላሉ፡፡

Post a Comment

0 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.