የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የሚያግዙ ነገሮች:-

የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የሚያግዙ ነገሮች:-

❖የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው ትልቁ ድክመት ሆኗል። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል።
❖ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት በቶሎ የሚሞሉ ሊቲየም አየን ባትሪዎችን ሲሆን ዲዛይናቸውም ባትሪዎቹ ተጠጋግተው እንዲቀመጡ የሚያደርግ ነው።
❖የስማርት ስልኮች ግፅታና ዲዛይን ቶሎ ቶሎ መቀያየር ማሻሻያውን እንዳከበደውም እየተነገረ ነው። በርግጠኝነት ይህ ነው የሚባል ነገር ባይኖርም የስማርት ስልኮችን እድሜ ለማርዘም የሚረዱ ነገሮች አሉ።
❶. ደካማ በይነ መረብ
ስልኮዎ በየሄዱበት ጥሩ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) መስመርን ለማግኘት ይሞክራል። በተለይም ደካማ የበይነ-መረብ አገልግሎት ባለበት ወይም አንድ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች የገመድ አልባ ኢንተርኔትን (ዋይ ፋይ) ለመጠቀም ሲሞክሩ ስልክዎ ሙከራውን ያከረዋል።
ምርጥ የሚባል መፍትሄ ባይሆንም ስልክዎን ኤርፕሌን ሞድ ላይ ማድረግ ጥሩ ኢንተርኔት ለማግኘት እየታገለ ያለው ስልክዎ ባትሪ እንዳይጨርስ ይረዳዋል።
❷. አንዳንድ መተግበሪያዎች (አፕልኬሽኖች)
አንዳንድ መተግበሪያዎች ባትሪ ይጨርሳሉ። ስለዚህ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎችን መዝጋት የባትሪን እድሜ ያረዝማል።
በተጨማሪም ባትሪ የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ባትሪ እየጨረሰ ያለውን መተግበሪያ መለየት ያስፈልጋል።
❸. ያሉበትን ቦታ አመልካች (ጂፒኤስ)
የቦታ አመልካችን (ጂፒኤስ) ማብራትም ባትሪ የሚጨርስ ነገር ነው። እንደ ትዊተር ያሉ አፕልኬሽኖች ደግሞ እርስዎ ሳያውቁት ሁሉ ያሉበትን ቦታ መዝግብው ይይዛሉ።
ስለዚህ ያሉበትን ቦታ የሚመዘግቡ መተግበሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ የማይፈልጓቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል።
❹.ከፍተኛ ሙቀት
ሊቲየም ባትሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጡ በደንብ አይሰሩም። ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው አየን ባትሪው ቶሎ ቶሎ ቻርጅ እንዲደረግ ያስገድዳልና።
ስለዚህ ስልክዎ ለከፍተኛ ሙቀት ወይም ለከፍተኛ ቅዝቃዜ እንዳይጋለጥ ማድረግ አይነተኛ መፍትሄ ነው።
❺. ትልልቅ ስክሪኖች
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስልኮች ትልልቅ ስክሪኖች እንዲኖራቸው እየተደረገ ነው። ይህ ትልቅ ስክሪን ሲከፈትና ሲበራ ባትሪ ይጨርሳል። ስለዚህም የስክሪኑን የብርሃን መጠን መቀነስ ጠቃሚ ነው።
ስክሪኑን ማጥፋትና ቶሎ ቶሎ ስልክዎን አለመመልከትም ሌላው መፍትሄ ነው።
❻. ከፍተኛ ድምፅ
የመተግበሪያዎች ወይም የስልክ ጥሪዎች ድምፅ ከፍተኛ ከሆነ ባትሪ ይጨርሳል። አብዛኛውን ጊዜ የድምፅ ነገር ስልክዎ ባለው ስፒከር የሚወሰን ይሆናል።
የጆሮ ማዳመጫ መጠቀምና በሚያዳምጡበት ወቅት የሌሎች መተግበሪያዎችን ድምፅ ማጥፋትም ጥሩ ነው።
❼. ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ
በፊት በፊት ስልክዎ ባትሪ እስኪጨርስ ከተጠቀሙ በኋላ ቻርጅ ማድረግ ነበር ተመራጩ። አሁን ግን ማድረግ የሚጠቅመው ተገላቢጦሹን ነው።
ይህ ማለት ደግሞ ከስር ከስር ባትሪ ሳይጨርስ ስልክን ቻርጅ ማድረግ መልካም ነው። ባትሪዎ መጠን ከግማሽ በታች ዝቅ እንዳይል ቻርጅ ቢያደርጉ የባትሪዎን እድሜ እንደሚያረዝም የሞባይል ስልኮች ባለሙያዎች ይመክራሉ።
እርግጠኛ መፍትሄዎች
❖ሁሉም የሞባይል አምራቾች የሚስማሙበት ዋነኛ መፍትሄ ስልክዎን ባትሪ ሃይል ቆጣቢ ሞድ ላይ ማድረግን ነው። ይህ ማለት ደግሞ የስልክዎ ስክሪን ብርሃን ይቀንሳል፣ ስልክዎ ንዝረት ያቆማል፣ ብዙ ማሳወቂያዎች (ኖቲፊኬሽን) አይደርስዎትም።

አዳዲስ መረጃዎችን   
                                 TESFA TECHNICAL
like እና share



Post a Comment

2 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.