በማህበራዊ ሚዲያዎች ልናጋራቸው የማይገቡ 10 ነገሮች

በማህበራዊ ሚዲያዎች ልናጋራቸው የማይገቡ 10 ነገሮች


በዘመናችን ቴክኖሎጂ ከወለዳቸው የማህበራዊ ሚዲያዎች አንዱና ዋንኛው ፌስቡክ ሲሆን ትኩስ፣ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ መረጃዎች በፌስቡክ እንደሚለቀቁ ሁሉ አወናባጅ፣ ወቅታዊ ያልሆኑና ለአሉታዊ አላማ የሚውሉ ይዘቶችም ይስተናገዱበታል። በመሆኑም በፌስቡክ ላይ የምናጋራቸው መረጃዎችን ከመልቀቃችን በፊት ደግመን ማሳብ እንዳለብን ልብ ይሏል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 10 ነገሮች ፌስቡክ ላይ ባያጋሩ (ሼር ባያደርጉ) ይመከራል።
1. ፓስፖርት ወይንም የመንጃ ፈቃዳችን ዝርዝር መረጃዎች የሚያሳዩ ምስሎችን ማጋራት መረጃዎቹን አመሳስለው በመጠቀም ህገ-ወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ሰዎች እጅ እንድንወድቅ ሊያደርገን ይችላል።
2. የበዓል እቅድ ቁጥሮች እና ሚስጢራዊ ኮዶችን ተጠቅሞ ሀሳብን ለመግለፅ መሞከር ለአደጋ የማጋለጥ እድሉ ዝቅተኛ ነው። ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የየእለት እቅዳችን ማጋራት ለአደጋ ሊያጋልጠን ይችላል። ለአብነትም “ለአንድ ሳምንት ለስራ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እየወጣሁ ነው” የሚል ፅሁፍ በፌስቡክ ገፃችን ላይ ብንለጥፍ ሌቦች አንድ እርምጃ እንዲራመዱ ፈቀድንላቸው ማለት ነው።
3. የባንክ ሂሳብ ደብተሮቻችን እና የቪዛ ካርዶችን ቁጥሮች እንዲሁም ተያያዥ መረጃዎች ለፌስቡክ ጓደኞቻችን ማጋራትም ለመረጃ መንታፊዎች ሊያጋልጠን ይችላል።
4. የሌሎች ሰዎችን የፈጠራ ውጤት የእኔ ነው ብሎ መለጠፍ
5. የህፃናትን ምስል መለለጠፍ
6. ስራ እና አለቃን የተመለከቱ ቅሬታዎች የስራቸውን ባህሪ እና ቀጣሪ ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ግልፅ ትችቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሰነዘሩ በርካታ ሰራተኞች ከስራ ተሰናብተዋል። ተጠያቂነት በሞላበት አሰራር ከላይኛው አመራር ባይደርስም በቅርባችን ከሚገኙ ሀላፊዎች ጋር ፊት ለፊት መነጋገሩ ተመራጭ ነው። በስራ ቦታ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማጋራት በቀጣሪ ድርጅቶች ዘንድ ጥሩ ስሜት ላይፈጥር ስለሚችል መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ከስራ ውጪም ማንኛውንም ሰው ማማት እና ግላዊ ጉዳዮቹን እያነሱ የቃላት ጥቃት መሰንዘርም ተጠያቂ ያደርጋል።
7. መታወቂያዎች (የነዋሪነት መታወቂያና ሌላ)
8. በቀጣይ ስለምንሳተፍባቸው ፕሮግራሞች “ነገ ምሽት ‘አዲስ’ የተሰኘውን አስቂኝ ቲያትር ለማየት እሄዳለሁ ብለን ፌስቡክ ላይ ለጓደኞቻችን ብናጋራ ጥሩ ጊዜ እንድናሳልፍ የሚመኙ እንዳሉ ሁሉ በዚያ ስአት እና ቦታ መጥፎ ነገር ሊያደርስብን ለሚችል ሰው ራሳችን አሳልፈን ሰጠን ማለት ነው።
9. በቅርበት የተነሱ ምስሎች ምንም እንኳን ግላዊ (ፕራይቬሲ) ሴቲንጋችን ጠንካራ ቢሆንም የፌስቡክ አድራሻችን በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በመረጃ ዘራፊዎች ሊሰበር ይችላል። በመሆኑም የምንፈልጋቸው ሰዎች ብቻ እንዲመለከቷቸው የለጠፍናቸው ምስሎች ሌሎችም ሰዎች ሊመለከቷቸው እና ለእኩይ ተግባር ሊጠቀሙባቸው ስለሚችሉ ባንለጥፋቸው ይመከራል።
10. የአሸናፊ ሎተሪ ምስሎች ብንለጥፍ ምናልባትም ራሳችንን አስፈላጊ ወዳልሆነ አደጋ መጋበዝ ሊሆን ስለሚችል ባንለጥፋቸው ይመከራል

Share and Like Comments
                       ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

ዌብሳይታችን 👉www.tesfatchnical.blogspot.com
ቴሌግራማችን 👉 http://t.me/Tesfatechnical Blog/
ፌስቡክ ፔጃችን 👉 http://facebook.com/tesfatechnical

Post a Comment

2 Comments
* Please Don't Spam Here. All the Comments are Reviewed by Admin.